Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 / ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ
  • opening dateበቀን-20/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8:30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Metals And Metal Working , Construction Materials And Raw Materials

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የማጠንከሪያ ብረት፣ የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-02/2019

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የማጠንከሪያ ብረት፣ የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የሚገዙ የማጠንከሪያ ብረት ፣ የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ10/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 20-/-02-/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ--10/-02-/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 20-/02/-2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 / ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን-20/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8:30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መሀተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድህረ ገፅ -www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

(ባህር ዳር)

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
Amhara Rural Roads Construction Agency seeks suppliers of reinforcement steel, bridge bearings and gabion for its road construction and maintenance works. Bidders must hold a valid trade licence, TIN, tax payment proof, and VAT registration if the purchase exceeds ETB 500,000.
Save Tender