Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
  • Address የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0467 71 11 80
  • Website
  • Deadline16 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-16 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 ዓ.ም በተፈቀደለት በጀት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ መስተወቂያ

 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 ዓ.ም በተፈቀደለት በጀት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

3.     በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በሕግ ያልተገደቡ፡፡

4.     የኤሌክትሮኒክስ ሰነድ ግዢ ለመፈፀም በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒከና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጅናል ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም፤ ስለ ተጫራቾች የንግድ ፊቃድ፣ የቫት ሰነድ፣ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው / ኦርጅናል ከሆነ ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡

7.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ታከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን፤ ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤ የመጨረሻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።

8.     ማንኛውም ተጫራች ሕጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢ.ፌ.ዴ. ሪ በክልሉ መንግሥት ሕጐች ተቀባይነት ያለው ኦርጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ ዋስትና(CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት።

10.  ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈለግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል።

11.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ 046 771 1180 / 046 771 0849 ዘወትር በሥራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

12.  ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

13.  የኤሌክትሮኒክስ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

የቢሮው አድራሻ፡- በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ ቢሮ።

ወራቤ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ

 

Save Tender