የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የመ/ቤቱ ሠራተኞችን ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ከህጋዊ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የመ/ቤቱ ሠራተኞችን ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ከህጋዊ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የጨረታውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000498682492 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ የባንክ ሲልፕ በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከጠቅላላ አገልግሎትና ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል ቀርባችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
መስፈርቶች-
1) በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ንግድ ሥራ ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት የታደሰ ምዝገባ ፍቃድ፣የግብር መክፊያ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት እና በማህበሩ ስም የታተመ ደረሰኝ ኮፒ ሠነድ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ካሉ ይበረተታሉ፤
2) ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ደረጃ (1) አንድ ሆኖ ባለ45 ወንበርና ከዚያ በላይ የሚችል ሆኖ ብዛት /1/ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተሽከርካሪ መሆን አለበት፡፡
3) ማህበሩ ለወድድር ሲቀርብ የማህበሩን ደረጃና ብቃት የሚገልጽ ወቅታዊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
4) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
5) የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ በአርባምንጭ ከተማው ውስጥ ባሉ በተመረጡ ፌርማታዎች ተንቀሳቅሶ በቀን ጠዋት 2 ዙር እና ከሰዓት 2 ዙር በአጠቃላይ በቀን 4 ዙር ወይም በቀን ውስጥ 50 ኪ.ሜትር ያህል ተንቀሳቅሶ አገልግሎት ለመስጠት የሚችል፡፡
6) የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ፡- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት።
7) ጨረታ የሚታሸግበት ቀን - ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፉ መ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
8) ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ የማህበሩ ክብ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለባቸው።
9) የመወዳደርያ ሰነድ የሚቀርበው በሰም በታሸገ ፖስታ ሲሆን በተጨማሪ የማህበሩ ክብ ማህተም በፖስታው ላይ መኖር አለበት፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
1. አሸናፊው ተጫራች ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀርበው ተሽከርካሪ ደረጃ (1) ብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የመድህን ዋስትና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከውል በፊት ማቅረብ አለበት፡፡
2. የነዳጅ ፍጆታ እና ሌሎች መሰል ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ከአቅራቢው ማህበር የሚሸፈን መሆኑን እናሳስባለን፡፡
3. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ጎን፡፡
ስልክ:- 0461811273/0461810380/0461810614/0461810539
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ
