የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለሚገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ፖምፖች፣ ጀነሬተሮች እና ተያያዥ እቃዎች ኮርፖሬሽኑ ባያያዘው ዝርዝር መግለጫ /specification/ መሰረት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
ፖምፖች፣ ጀነሬተሮች እና ተያያዥ እቃዎች ግዥ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር WWC/KMCO/NCB01/2018
የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለሚገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ፖምፖች፣ ጀነሬተሮች እና ተያያዥ እቃዎች ኮርፖሬሽኑ ባያያዘው ዝርዝር መግለጫ /specification/ መሰረት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ።
1. ህጋዊና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የተጠየቁትን ፓምፖች፣ ጀነሬተሮች እና ተያያዥ እቃዎች አባሪ በተደረገው ዝርዝርመግለጫ /Technical specification/ መሰረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
3. የሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሕጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
4. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የእቃ እና አቅርቦቱ ኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገቢ እስኪሆን ድረስ ከአቅርቦቱ ጋር የተያያዙ ማንኛውም ወጪዎች ማለትም ማጓጓዣ የጫኝ አውራጅ እና ታክስ በተሰጠው ዋጋ ላይ ተጠቃለው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. በዚህ ጨረታ የሚሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ወር /ለ60 ቀናት/ የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የተጠየቁትን ፓምፖች፣ ጀነሬተሮች እና ተያያዥ እቃዎች የሚያቀርቡበት ጊዜ ውል ከተያዘ ጀምሮ /Delivery Time/ በ30 /በሰላሳ/ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
7. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋና እና ኮፒ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል /ለየብቻ/ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ቴክኒካል የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፣ ሲፒኦ፣ የእቃ ዝርዝር መግለጫ እና ተየያዥ ሰነዶች በአንድ ፖስታ ማቅረብ እንዲሁም በሁለተኛው ፖስታ የፋይናንስ ሠነድ ለብቻ በማዘጋጀት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል በአካል በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ቀን ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
9. ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ከተመረጠ በራሱ ወጪ እቃዎችን ኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግቢ ያቀርባል፡፡
10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ያለ ቅድመ ሁኔታ ለግዥ የሚከፈል የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኮርፖሬሽኑ ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
12. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 (ሃያ) ተከታታይቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኮርፖሬሽናችን ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክበተከፈተ የሂሳብ ቁጥር 1000265163223 ገቢ በማድረግ እና የባንክ ገቢ ማረጋገጫ በማቅረብ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይንም ኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚገባው አዲስ አበባ ማ/ጽ/ቤት ሲሆን የሚከፈተው አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል ይሆናል፡፡
13. የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡ ለወደፊቱም ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ሌሎች ጨረታዎች ላይ አይሳተፉም፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/በኮርፖሬሽኑ ስም በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት ውል ያልያዘ እንደሆነ ኮርፖሬሽኑ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
15. የእቃዎቹ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ ይችላል፡፡
16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡:
ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልከ ቁጥር፡- 0953281222/011-443-25-95 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ ፋክስ ቁጥር፡-033-551-3569 ፖሳቁ 35
በውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
