የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል Heavy Duty Scanner በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል Heavy Duty Scanner በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በውድድር መስፈርት መሠረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የአቅርቦት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ 15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በCPO ወይም ህጋዊ ባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) 190 ቀን ፀንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
5. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ለ3 ወራት (90 ቀናት) ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
7. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።
8. ተጫራቾች በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0462121455/ 0462122050
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
