የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
• ሎት 1፡- ሰርቨር
• ሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች
በዚሁ መሰረት ከላይ ለተጠቀሱ ዕቃዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡-
1. የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. ያልታገደ የንግድ ፍቃድ ወይም ታግዶ የነበረ ከሆነ የእገዳ ጊዜውን ስለመጨረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው 4ኛ ፎቅ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሰርቨር 60,000 (ስልሳ ሺህ)፣ ለኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
9. የጨረታው አሸናፊዎች በውሉ መሠረት ግዥ የሚፈጸምባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ እቅርበው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የመ/ቤቱ አድራሻ፡- በሲዳማ ከልል ሀዋሳ ከተማ፤ ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (SBC) ቢሮ ጀርባ ባለው የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ፡፡
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 046-212-71-38
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
