በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና ቢሮ መገልገያ እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስተወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና ቢሮ መገልገያ እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃዎችን ሁኔታ ከደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ግቢ በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 2፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ 2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20% ያላነሱ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (cpo) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርበታል፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት አስተዳደርና ፋይናስ ቡድን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ በሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
4. የተጫራቹ አሸናፊም እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወይም (cpo) ለተሸናፊዎች ይመለሳል፡፡
5. በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ ለሁሉም እንደተገለፀ አስፈላጊውን ውል በአካል ቀርቦ መፈረም አለበት ይህ ባይፈፀም የጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ የማይመለስ መሆኑን እና ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000024297873 በደ/ማ/መ/አውታር አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ በደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ቁጥር 08 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
7. ማንኛውም ተጫራቾች የሰጠው መወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ ግምገማ ተጠናቆ የጨረታ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል። አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0587781350 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
