Tender Detail

Tender Details

  • Company በስልጤ ልማት ማህበር የሃይረንሲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ጽ/ቤት
  • Address በስልጤ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0467 71 04 62
  • Website
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ለ2ኛው መንፈቀ ዓመት ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

በስልጤ ልማት ማህበር የሃይረንሲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ  

 

በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ለ2ኛው መንፈቀ ዓመት ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

     የዕቃዎቹ ዝርዝር                                                      የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO መጠን

1.     ለጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና የባልትና ዕቃዎች - - - - - - - - - ብር 5,000.00

2.     ጥሬ ስጋ - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - ብር 3,000.00

3.     ለጤፍ ዱቄት - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - ብር 5,000.00                   

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

1.     በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፍቃድና የስራ ልምድ ያላቸው።

2.     የዘመኑን የሥራ ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ።

3.     የቲን ቁጥር ያላቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4.     የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO በሚወዳደሩበት ዕቃ በተጠየቀው መጠን ማስያዝ አለባቸው።

6.     አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን እስከ ሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችል።

7.     ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

8.     ከአንድ በላይ በሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደር አቅራቢ በእያንዳንዱ በሚወዳደርባቸው ዕቃዎች የተጠየቀውን CPO ማስያዝ ይኖርበታል።

9.     ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 9፡30 በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሳምንት መጨረሻ ቀናት ወይንም የበአል ቀናት ላይ ካረፈ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሰም የታሸገ ፖስታ ሆኖ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።

11. የሚቀርበው ሰነድ በዋና እና በኮፒ መሆን ይኖርበታል።

12. ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

13. ተጫራቾች ሆኑ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚያስቀራቸው ነገር ሊኖር አይችልም።

14. ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ መጀመር የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467 71 04 62 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በስልጤ ልማት ማህበር የሃይረንሲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ጽ/ቤት

Save Tender