በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት በምስራቅ ወለጋ በምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና ቄለም ወለጋ ዲስትሪክት ሥር የሚገኘውን የቁም ባሕር ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ወለጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
OFWE/WB/Bar 02/2018
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት በምስራቅ ወለጋ በምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና ቄለም ወለጋ ዲስትሪክት ሥር የሚገኘውን የቁም ባሕር ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. የጊንድላ፤ የአጣና የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጊምቢ ከተማ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ወለጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
2. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0577711750 መደወል ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
ወለጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
