የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈ ከሣሽ 1ኛ/ አቶ አሸብር መሉጌታ 2ኛ/አቶ ዮናስ እሸቱ እና በአፈ ተከሣሽ አቶ መንግሥቱ ተስፋዬ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሣሽ ንብረት የሆነው 200 ካ.ሜ የሆነ ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ ከሣሽ 1ኛ/ አቶ አሸብር መሉጌታ 2ኛ/አቶ ዮናስ እሸቱ እና በአፈ ተከሣሽ አቶ መንግሥቱ ተስፋዬ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሣሽ ንብረት የሆነው በደነባ ከተማ 01 ቀበሌ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ዮሐንስ፣ በሰሜን ፍቅርተ ታደሰ እና በደቡብ መንገድ የሚያዋስኑት 200 ካሜ ቦታ ላይ የሚገኘውን ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ 1,293,955.61 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ አምስት ብር ከስልሣ አንድ ሣንቲም/ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በመሆኑም፡-
1. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 1/4ኛውን ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ የዋስትና ወረቀት ወይም በሲፒኦ ወዲያውኑ ለሐራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።
4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በሕግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል። በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሐራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
(ደ/ብርሃን)
