Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
  • Address ሆሳና ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +46 8 21 01 83
  • Website
  • Deadline10 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-10 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Stationery Materials , Electronics Materials

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ለ 2018 በጀት ዓመት ግዥ ከዚህ በታች በሎት የተቀመጠውን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ለ 2018 በጀት ዓመት ግዥ ከዚህ በታች በሎት የተቀመጠውን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት1. ስቴሽነሪ፣ ሎት2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት3. የልደት ክብር መዝገብ ህትመት

ስለሆነም፡-

1.     በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     በመስኩ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

በዚሁ መሠረት ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል እንድትገዙ፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ግዢ መጠን 3% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ኤጀንሲው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመመላትና የድርጅታችሁን ማህተም በማሳረፍ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነድ ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ መቅረብ ያለበት ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን ቴክኒካል ሠነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን ቴክኒካል ያለፈ ብቻ ለፋይናንሻል የሚወዳደሩ ይሆናሉ። የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሳብ መቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላሳዩ ግዢዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈጸሚ ይሆናል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በ8፡30 ሠዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፍታል ፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ፡- አድራሻ የማ/ኢት/ክ/መ/ወ/ኩ/ም/ኤ ቢሮ ቁጥር 05 ቀርቦ በአካል ማነጋገር ይቻላል።

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ

Save Tender