Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline03 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-03 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Raw Materials

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለፋብሪካው ለምርት ግብዓትነት የሚጠቅመውን 40 ቶን ግሉ ፓውደር Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ካምፓኒያችን የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ብርሃን ረጂዎፖሊታን ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ሲሆን በዋናነት ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕለይ ውድ ጣውላ እያመረተ መሆኑ ይታወቃል ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት በግብዓትነት የሚጠቅመውን 40 ቶን ግሉ ፓውደር Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት

1.     በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው

3.     የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5.     የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፤

6.     ተጫራቾች ለግሉ ፓውደር ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7.     ተጫራቾች በሚያተርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው

8.     በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፣

9.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡

11. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለግሉ ጨረታ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ እንዲሁም በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

13. ከተጠቀሰው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት ውጤት አያስገኝም፡፡

14. አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረክባል፡፡

15. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 637 5803 ደውለው ይጠይቁ።

 

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

Save Tender