ዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለውጪ ገበያ ያዘጋጀውን 450 ኪሎ ግራም የኮረሪማ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋይ.ዲ.ኤስ.ኤል 01-2018
ዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለውጪ ገበያ ያዘጋጀውን 450 ኪሎ ግራም የኮረሪማ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (ብር 200.00) በመክፈል አሌክሳንደር ፑሽኪን ጎዳና ከቄራ ወደ ሳር ቤቶች በሚወስደው መንገድ ሳልቫቶሪና ቤተሰቦቹ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አካባቢ ሀይለማሪያም ወልዴ ህንፃ ወይም ቴምር ፕሮፐርቲስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጎን ባለ ህንፃ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03/05 እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
3. ተጫራቾች በጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ሲፒኦ በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እሰከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን ዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
4. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስራ አምስት (15) ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤
5. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
09-43-03-14-48 / 09-11-55-87-52
አዲስ አበባ
ዋይ ዲ ኤስ ኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
