በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚኒባስ መኪና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚኒባስ መኪና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ የተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት 12ና ከዚያ በላይ መቀመጫ ያለው በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ ተሽከርካሪ ኮድ - 3 የሆነ ሦስተኛ ወገን /መድን ኢንሹራንስ/ ሽፋን የተገባለት፣
2. ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያደረገና የታደሰ ሊብሬ ማቅረብ የሚችል፤
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በአቃቂ ቃሊቲ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 7ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጽ/ቤታችን አስተዳደርና ፋይናንስና ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት የጨረታ ሳጥኑ በሰባተኛው (7ኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅ/ፅ/ቤቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ በጥንቃቄ በመሙላት የተሟላ ቴክኒካል ሰነድ፣ ፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በሰም በማሸግ በአጠቃላይ ሦስት (3) ፖስታዎችን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. /C.P.O/ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማስገባት አለበት፣
7. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል።
8. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት የክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 09 13 17 23 43 እና 09 12 04 67 72 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
