Tender Detail

Tender Details

  • Company መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
  • Address ሲዳሞ ተራ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112-31-31-47
  • Website
  • Deadline23 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-23 00:00:00
  • Categories Rent

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት /ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል የሕንፃ ቦታ ኪራይ ጨረታ

 

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት /ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ፡-

1.       ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በአክሲዮኑ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረግ መርካቶ ሲዳሞ ተራ የማኅበሩ ሕንፃ በሚገኝበት 4ኛ ፎቅ ላይ ዘወትር በሥራ ቀናት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

2.       ጨረታው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።

3.       ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አከሲዮንማኅበሩ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር M433 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.       ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

- ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስስክ ቁጥር፡-011 231 3147/ 011 231 3237, 011 872 2926 ወይም በአካል ሲዳሞ ተራ መተሳሰብ የገበያ ማዕከል መጠየቅ ይችላሉ።

 

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Save Tender