በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የኦከስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና የአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የኦከስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና የአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1፡- የደንብ ልብስ፣ የሠራተኞች ጥቅማጥቅምና የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2294
ሎት 2፡- የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2528
ሎት 3፡- ለአላቂ የሕከምና ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 750
ሎት 4- ለአላቂ የትምህርት እቃዎች መግዣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1471
ሎት 5፡- አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች ማስከበሪያ ብር 998
ሎት 6፡ ለተለያዩ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 506
ሎት 7- ለፕላንት ማሽነሪ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2996
ሎት 8፡ ለፈርኒቸር/የቢሮ ዕቃዎች/ ማስከበሪያ ብር 1265
ስለሆነም-
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በሥራ ሰዓት በኦከስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመቅረብ በማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ መግዛት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች አምራች ለሆኑ የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው: -
ሀ/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
ለ/ በመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
ሐ/ በተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
መ/ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ የአምራችነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በሲፒኦ በኦክስፋም
ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
6. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤት በማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ መምህራን ማረፍያ ይከፈታል፡፡ የጨረታው ቀን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበትና ናሙና ለሚያቀርቡባቸው የዕቃ ዓይነት ከመስሪያ ቤታቸው በቀረበው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ የአዲስ ፍረ የመጀ/ደ/ት/ቤት 5ኛ ፖሊስ ጣብያ ወረድ ብሎ ልዩ ስሙ ሰሳሴ ወፍጮ ቤት ገባ ብሎ
ስተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0115-51-58-61/ 0118-68-56-98
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት የኦክስፋም ቅድመአንደኛ ት/ቤት እና አዲስ ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
