Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-05 00:00:00
  • Categories Rent

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ/ የድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አገ/07/06/2018 በኪራይ የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል ፡፡


14ኛ ዙር የንግድ/የድርጅት ቤቶች ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ /አገ/07/06/2018

 

1.       የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ/ የድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አገ/07/06/2018 በኪራይ የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል ፡፡

2.       ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ /የድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.       ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በፌዴራላዊ መንግስት ባለቤትነት በተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ነው፡፡

4.       የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር / በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በኮርፓሬሽኑ ቅ/ፅ/ቤቶች በኩል በአካል በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡

5.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢያ አዳራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከየካቲት 24 እስከ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ሶስት የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል አንድ ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል ፡፡

6.       ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ሥራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡

7.       ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-22-49-18-85 / 09-10-48-59-48 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዌብሳይት/Website WWW.agh.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ P.O.Box 299

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender