የአፈጻጸም ከሳሽ ራቢያ ጃፈር እና የአፈጻጸም ተከሳሽ ሐጂ መንሱር መሐመድ እና የአፈጻጸም ተከሳሽ ነኢማ ሙክታር መካከል ያለውን አፈጻጸም ጉዳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ክተማ ወረዳ 3 ውስጥ ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የሚገኘውን የመኖሪያ እና የንግድ ቤት የሚሸጥ ስለሆነ ለመግዛት የሚፈልግ ሰው በቦታው ተገኝቶ መግዛት የሚችል መሆኑን የምስራቅ ወለ
በነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የፍትሐብሔር ችሎት ቡድን
የ2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈጻጸም ከሳሽ ራቢያ ጃፈር እና የአፈጻጸም ተከሳሽ ሐጂ መንሱር መሐመድ እና የአፈጻጸም ተከሳሽ ነኢማ ሙክታር መካከል ያለውን አፈጻጸም ጉዳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርኮልፌ ቀራኒዮ ከክተማ ወረዳ 3 ውስጥ ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር ተብሎ በሚታወቅ የሚገኝ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት አዋሳኝ በምስራቅ ተካ አሰፋ እና ብርሃኑ ደስታ፤ በምዕራብ ሙሃመድ፣ በሰሜን የመኪና መንገድ፤ በደቡብ ከድር መሐመድ መካከል የሚገኝ የመሬት ስፋት 766ሜ2 ካሬ የሆነ በባለሙያ ግምት በ661,824 (ስድስት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃያ አራት) ብር ተገምቶ የቀረበውን መነሻ በማድረግ ለ2ኛ ጊዜ ተካሂዶ የነበረው የጨረታ ማስታወቂያ ውድቅ ስለሆነ በፍትሓብሔር ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 428(1) ከፍተኛ ጨረታ ክፍያ ለከፈለ ተወዳዳሪ ተሽጦ የ2ኛ ዙር ጨረታ በድጋሚ እንዲካሄድ በቀን 04/07/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 አንስቶ እስከ ከቀኑ 6:30 ድረስ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ ግለሰቦች የጨረታውን 1/4ኛ በማስያዝ በዚህ ቤት ቦታ ላይጨረታው ስለሚካሄድ ይህንን ቤት መግዛት የምትፈልጉ ተወዳድራችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን በመግለጽ በምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ያሳውቃል፡፡
የዚህ ጨረታ ማስታወቂያ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተወዳዳሪዎች በሲንቄ ባንክ የነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሂሳብ ቁጥር 1079807071216 በሆነ ላይ በሲፒኦ አስይዛችሁ መወዳደር እንደምትችሉ የነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አዟል።
የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ በኋላ በዛው ቅጽበት ያሸነፈበትን ገንዘብ ከአጠቃላዩ 1/4ውን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሂሳብ ቁጥር ላይ አስቀድሞ ገቢ አድርጎ እንዲተርብ የነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አዟል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ቤት ተወዳድራችሁ መግዛት የምትፈልጉ ግለሰቦች ይህ ንብረት የሚገኝበትን ለማወቅ በስልክ ቁጥር 0911805727 ላይ በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የፍትሓብሔር ጉዳይ ችሎት
