የአብክመ ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርብ
3. ከላይ በተቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፣
6. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል/በፋይናንስ ህንጻ በ16ኛ ቀን 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆን በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
9. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል፡፡
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ግዥ ክፍል ደረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃወች በራስ ወጭ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
የአብክመ ጤና ቢሮ
ባህር ዳር
