የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መዕረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች።
2. በዘርፋ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
4. የግብር ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ።
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
6. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓት 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፈል ከደ/በ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 /አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) አርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ (1) አርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ'ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
12. ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚው ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ፡- 0966886973/0917503586/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት
