የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ ባለ መብቶች እነ ወ/ሮ ጉዶ ጉተማ 4 ሰዎች እና በፍርድ ባለ ዕዳ ወ/ሮ አየለች ጉተማ መካከል ስላለው በፍርድ አፈፃፀም ክርክር የአውራሽ ወ/ሮ ጌራወርቅ ቦጋለ ንብረት የሆነው ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ የወሰነ ሲሆን መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በጨረታ ተወዳድራቹ እንድትገዙ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለ መብቶች እነ ወ/ሮ ጉዶ ጉተማ 4 ሰዎች እና በፍርድ ባለ ዕዳ ወ/ሮ አየለች ጉተማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ክርክር የአውራሽ ወ/ሮ ጌራወርቅ ቦጋለ ንብረት የሆነው በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጢያ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ በ184 ካሬ ሜትር ላይ ተገንብቶ የሚገኝ ቤት አዋሳኞቹ በምስራቅ የገበያ ቦታ፣ በምዕራብ አየለች ጉተማ፣ በደቡብ መንገድ እና በሰሜን በየሺ ታደሰ የሚዋሰን በወራሾች ድርሻ ምክንያት በጨረታ ለመሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ስላስተላለፈ የጨረታው መነሻ ዋጋ ብር 96,000 (ዘጠና ስድስት ሺህ) በማለት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለ30 ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በቀን 09/07/2018 ዓ.ም. ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው የሚካሄድ መሆኑን እና መግዛት የሚፈልጉ ሰዎች ለጨረታው ምክንያት የሆነው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ በመቅረብ ተወዳድረው እንዲገዙ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
