Tender Detail

Tender Details

  • Company አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251914340031
  • Website
  • Deadline15 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-16 00:00:00
  • Categories Building Materials , Steel, Metals And Aluminium , Construction Materials And Raw Materials

ኩባንያችን አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የአርማታ ብረት እና EGA ቆርቆሮ ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የአርማታ ብረት እና EGA ቆርቆሮ ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

1.     በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፣

2.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

3.     የአርማታ ብረት እና EGA ቆርቆሮ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

4.     የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

5.     ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። በተጨማሪም አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አማራ ልማት ማህበር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 መውሰድ ይችላሉ፣

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፣

7.     ግዥው በሦስት ሎት የተከፈለ ሲሆን፤ ተጫራቾች በአንድ ወይም በሁለቱ ወይም በሦስቱም ሎቶች መሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 07 አማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት በሚገኘው የአልማኮ ህንጻ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሎጅስቲክስ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።

9.     ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ7ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳረሽ ይከፈታል። ሆኖም 7ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

10. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊ መሆኑ በኩባንያችን ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈረም አለበት፣

11. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈውን ዕቃ ፕሮጀክት ሳይት ላይ በማቅረብ፤ ያቀረበው ዕቃ ላቦራቶሪ ቴስት ተወስዶ የሚፈለገውን ስታንዳርድ ማለፍ መቻል አለበት። ይህ ካልሆነ አቅራቢ ድርጅቱ በራሱ ወጪ ያቀረበውን ዕቃ መልሶ የሚወስድ ግዴታ ያለበት ሲሆን፤ በምትኩ ቴስት የሚያልፍ ዕቃ ከሶስት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፣

12. የኤጋ ቆርቆሮ ጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኩባንያው ማለትም አማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኘው ፕሮጀክት ሳይት በማጓጓዝ ማስረከብ አለበት፣

13. የአርማታ ብረት ጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኩባንያው ማለትም አማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኘው ፕሮጀክት ሳይት በማጓጓዝ ማስረከብ አለበት።

14. ኩባንያው በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች +251914340031/+251907294575 ባህር ዳር /ኢትዮጵያ መደወል ይቻላል።

 

አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender