Tender Detail

Tender Details


በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ2 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


2ኛ ዙር ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ2 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች

1 የደንብ ልብስ ግዥ

2. ለአላቂ የቢሮ እቃዎች

3. ለህትመት

4. ለአላቂ የት/ት እቃዎች

 5. አላቂ የጽዳትእና ሌሎች ዕቃዎች

6. ለተለያዩ አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች

7. ቋሚ የኤሊክትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ

8. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን

መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል ፡፡

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርመመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡

2. የገቢዎችእና ጉምሩክ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ፡፡

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት (ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡

5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእየንዳዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር/ አንድ መቶ ብር/በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለio ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

6.የጨረታ ማሰከበሪያ ለሁሉም ሎቶች 20,000 ብር (ሃያ ሺብር) በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ አለበት፡፡

7.የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡

8.የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ፡ በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው ::

9.አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት፡፡

10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ከፍል ሲያስረከቡና በጥራት ኮሜቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኃላ ይከፍላቸዋል፡፡

11.የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

12.የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ CPO በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ሁሉም ተጫራቾች ከ ጥር 1 ጀምሮ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን ባወጠው መመሪያ መሰረት ካሽ ሪጅሰተር ያለው ወይም QR ኮድ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባችው፡፡

አድራሻ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል በመናፈሻ ፊትለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር -

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender