Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-22 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጡ የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በሴፍቲኔት በጀት ላብቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጡ የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በሴፍቲኔት በጀት ላብቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.     የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችል

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው

3.     የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወቅት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾት አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገጽ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት፡፡

7.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡

9.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ /መጫረቻ ሰነድ ከ30/5/2018 እስከ 14/6/2018 የሰሜን ወሎ ዞን ዓ.ም ድረስ በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡

10. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ15/6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታቸው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሠረት ተገዥ የመሆን /የመቀበል ግዴታ አለባቸው፡፡

11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡

12. የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ /ኦርጅናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡

14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ /ስርዝ ድልዝ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ-

•        ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0333311597/2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

•        ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነለትን ነገር ደውሎ ግልጽ ካልሆነለት በስተቀር ያለአግባቡ ዋጋ መሙላት የለበትም፡፡ በኋላ ለሚያቀርበው ጥያቄ የማይቀበልና የተቋሙ ሃሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እናሳስባለን፡፡

 

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ

Save Tender