የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 2ኛ የሞተር ሳይክል ግዥ እና 3ኛ የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 2ኛ የሞተር ሳይክል ግዥ እና 3ኛ የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-
1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቲን ነምበር ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታክስ ክሊራንስ ሊኖራቸው ይገባል። በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በLetter of credit ወይም በካሽ ለእያንዳንዱ ግዥ በተናተጠል ከዚህ በታች ከተቁ 1 እስከ 3 በተቀመጠው መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ብር 25,000
2. የሞተር ሳይክል ግዥ ብር 30,000
3. የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ ብር 20,000
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
5. ከተቁ 1 እስከ 3 ሉተቀመጡት ለእያንዳንዳቸው ግዥዎች በመለያየት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን በአንድ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለያየት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
6. ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚህ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ላይ ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ላይ ተጫራች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።
8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
9. ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የግዥ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስተ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-145-67-77 ወይም 046-115-06-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
