የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የዞን ፋይናንስ መምሪያ G+1 ህንፃ ቀሪ ሥራ ለማስገንባት ይፈልጋል።
የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ዱራሜ
ግልጽ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018 ከዞፋመ
የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የዞን ፋይናንስ መምሪያ G+1 ህንፃ ቀሪ ሥራ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር ለመከላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
በፋይናንስ ቢሮ በአቅራቢነት ኦንላይን የተመዘገበ ወይም e-GP የተመዘገበ መሆን አለበት፤
የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ፋይናንስ ተቋም 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ብቻ በመመሪያ የተፈቃዱ ዋስትና ዓይነቶችን ማቅረብ የሚችል፣
ተጫራቾች በግንባታ ጨረታ ለመወዳደር የሚያበቃ ሙያ ፈቃድ ደረጃ GC-5/BC ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
ተጫራቾች ለግንባታ ጨረታ ለማወዳደር የሚያበቃ ሙያ ፈቃድ ደረጃ GC-5/BC-5 ከዚያ በላይ መሆን አለበት፤
ተጫራቾች ለግንባታ ጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 15 በማቅረብ መግዛት ይቻላል፣
ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የሚቀርቡትን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
ጨረታ በ21ኛ ቀን 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 9፡15 ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ይከፈታል። ሆኖም ግን ቀኑ በዓል/የዕረፍት/ ቀናት ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 046-554-0360 መደወል ይቻላል።
የከምባታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ዱራሜ
