Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ማ/ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል
  • Address ደ/ማርቆስ ከተማ አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058-178-10-73
  • Website
  • Deadline17 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-17 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Electronics Materials

በአብክመ የሙያ ብ/ም/ማ ኤጀንሲ የደ/ማ/ክ/ማዕከል ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደ/ማ/ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ የሙያ ብ/ም/ማ ኤጀንሲ የደ/ማ/ክ/ማዕከል ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1.     በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ

3.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው

4.     የግዥው ጠቅላላ መጠን ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ

5.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ. ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6.     የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከዋና ገ/ያዥ ላይ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ማ/የሙ/ብ/ም/ማ/ከ/ማዕከል ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን በ 8፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ካልተገኙም በኮሚቴው ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ ሰአቱ እንደተጠበቀ የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ቀን በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።

11. ተጫራቾች ክላስተሩ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡

12. የጨረታው ውድድር የሚታየው ክላስተሩ ባወጣው ዝርዝር መሰረት በጥቅል ዋጋ /በሎት/ ይሆናል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. በጨረታ የሚሳተፉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁ/ 058 178 10-73 / 058 178 71 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ቢሮአችን ደ/ማርቆስ ከተማ አምባሰል ህንጻ 5ተኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡

 

 

በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል

Save Tender