በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክልና ዴስክቶፕ ኮምፒውተር በውስን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
በድጋሚ የወጣ ውስን ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ተራ.ቁ 05/2018 ዓ.ም
በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክልና ዴስክቶፕ ኮምፒውተር በውስን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማሟላት ያለባቸው
1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድና TIN NO ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይታሸግና ወዲያውኑ በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
5. 15% /VAT ተመዝጋቢ መሆን አለበት
6. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ለይተው በሁለት ፖስታ በማድረግ በሰም ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
7. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ አንቀፅና ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላሣዩ ግዥዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
8. የቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳቦች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፀንቶ የሚቆይ ማስተካከያ የማይደረግባቸው መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡፡
9. ጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ሽያጭ 2% ብር ከባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለበት።
10. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከኤጀንሲው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፡፡
11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ከዚህ የመወዲደርያ ሀሳብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ የቀረበ ተጨማሪ ሠነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል። ጨረታ ሠነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፈርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው ማወዳደሪያ ሀሳብ ይሠረዛል።
አድራሻ በኢምግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጎን
ሀዋሳ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916020865/0916516908 ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
