Tender Detail

Tender Details

  • Company SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
  • Address ሀዋሳ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461228084
  • Website
  • Deadline08 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-09 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ባለኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ባለኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት መጫረት የሚችሉት፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ታክስ ክሊራንስ፤ የቲን ተመዝጋቢና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2.     ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀው ዝርዝር መግለጫዎች የያዘ ሠነድ (specification) በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡

3.     የጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማሳረፍ ባለኤሌከትሪከ ሞተር ሳይክል ዋጋ በሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ በማሳወቅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ11ኛው ቀን ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግ/ክ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4.     ጨረታው 6፡00 ሰዓት ታሸጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ CPO ወይም አንኮንዲሽናል የባንከ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።

6.     ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.     የጨረታ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

8.     ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

9.     የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ግ/ክ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ሕንፃ 04 ከፍል 27 ማግኘት ይቻላል፡፡

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ 046 2126783

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Save Tender