Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
  • Address የጨፋ ሮቢት ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0919930123
  • Website
  • Deadline10 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-11 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 እንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በጨፋ ሮቢት ከተማ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት 1,400 ካሬ ሜትር የመኖሪያ 2,130 ካሬ ሜትር ጠቅላላ ስፋታቸው 3,530 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅትና

በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 እንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በጨፋ ሮቢት ከተማ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት 1,400 ካሬ ሜትር የመኖሪያ 2,130 ካሬ ሜትር ጠቅላላ ስፋታቸው 3,530 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅትና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     የጨረታውን ሰነድ በጨፋ ሮቢት ከተማ እስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔሲፊኬሽን Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡

4.     ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

5.     ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ በአብከመ በአ/ብ/ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ20/05/2018 እስከ 03/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ03/06/2018 ዓ.ም 11:30 ሰዓት ይሆናል፡፡

7.     ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ04/06/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.     ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መ/ል/ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡

9.     የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0919930123/0910788122 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender