Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-17 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ከራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴከኒክ ማዕከል በመገኘት ከጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION) ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው።

ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒከ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ፣የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረክቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ። የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በ ሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ

ቁጥር 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Save Tender