Tender Detail

Tender Details

  • Company Dredawa Administration Government Communications Office (የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)
  • Address Dredawa, Phone: 0252-11-60-62
  • Website
  • Deadline10 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-10 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2018 በጀት አመት ከመንግስት በተመደበ በጀት የሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Dredawa Administration Government Communications Office (የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁመኮ 06/2018

 

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2018 በጀት አመት ከመንግስት በተመደበ በጀት የሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ መሣርያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1.     ተጫራቾች በኤሌክትሮኒክስ የተሠማሩና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የዘመኑን ግብር የከፈሎና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣

4.     ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን የህትመት አይነቶች ሳምፕል የሚጠይቁ በሆኑት ከዚህ በፊት በድርጅታቸው የሰሯቸውን ለሳምፕል ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሸግበት እለትና ሰአት ቀደም ብሎ የጨረታ ሠነዱን ከቢሮው የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር ዘ2 ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች አስፈላጊውን የቴክኒካል እና የፋይናንስ ሰነድ ለብቻ ለብቻ በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

7.     የጨረታ ሳጥኑ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በሥራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፤

8.     ተጫራቾች ብር 30,000 ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በጥሬ ገንዘብ በባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ለብቻው በአንድ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

 

የስልክ ቁጥር 0252-11-60-62

0948597011

 

የድ/ዳ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ድሬዳዋ

Save Tender