Tender Detail

Tender Details

  • Company ኤረር የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
  • Address ቢሾፍቱ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114335665
  • Website
  • Deadline20 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-20 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ኤረር የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ


የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የፅሕፈት መሣሪያዎች፤

ሎት-2 የጽዳት እቃዎች እና

ሎት-3 የደንብ ልብስ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በየሎቱ በመከፈል ጨረታ ሰነዱን ከአሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ/ ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ ቲን፤ ቫት፤ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፤ ሲፒአ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 5% (አምስት ፐርሰንት) በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) የድርጅቱን ማሕተም በመምታት ከዶክመንት ጋር ለብቻው ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

4. የሁለት ዓመት ኦዲት ሪፖርት 2016 እና 2017 ማቅረብ የሚችል እና ሁለት ሚሊዮን (2,000,000) የሚያሳይ"ባንክ እስቴትመት ማቅረብ የሚችል፡፡

5. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት

* ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) የድርጅቱን ማህተም በመምታት በ22ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

*ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡

የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡

“ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

* ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ከ ጎን OACF ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ:- 0910645442

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ

Save Tender