Tender Detail

Tender Details


በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች ግዢ በጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ እናጥገና

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች ግዢ እናጥገና

1. የፅህፈት መሳሪያ (ሎት 1) 6 የህንፃ መሳሪያ (ሎት 6)

2. የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 2) 7. የኤሌክትሮኒከስ ጥገኛ /ሎት 7/

3. የህከምና ቁሳቁስ (ሎት 3) 8. የደንብ ልብስ(ሎት8)

4. ኤሌክትሮኒከስ (ሎት 4)

5. ፈርኒቸር (ሎት 5)

በጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት

•         አቅራቢው የተሠማራበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣

•         የዘመኑን ግብር መከፈሉን የሚገልጽ ማስረጃ፣

•         የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/፣

•         ከተሰማራበት ዘርፍጋር በተያያዘ ስለተሰማራበት የሙያ ዘርፍ አቅራቢነት በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ፣

•         የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚግለጽ መረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ስሚያቀርቡት አጠቃላይ

•         የጽህፈት መሳሪያ (ሎት1) ብር 5,000

•         የፅዳት እቃዎች (ሎት2) ብር 5000

•         የህከምና ቁሳቁስ (ሎት 3) ብር 15,000

•         ኤሌክትሮኒከስ (ሎት4) ብር 15000

•         ፈርኒቸር (ሎት 5) ብር 10,000

•         የህንፃ መሳሪያ (ሎት6) ብር 10,000.00

•         የኤሌከትሮኒከስ ጥገና(ሎት7) ብር5,000.00

•         የደብ ልብስ (ሎ ት8) ብር20,000.00

•         ሀ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም

•         ለ/ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም

•         ሐ/ በሲፒኦ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የከፍያ ትዕዛዝ ህጋዊ ማህተም ያለው ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በቂ ዋስትናና ለዋስትና ሊበቁ የሚችሉ ማስያዣዎች 10% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይእስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመያዝ ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካውንት ቁጥር1000040517964 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫስ በማቅረብ ግዢ ንብረት አስተዳደርዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የፋይናሻልና ቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በሰም ኤንቨሎፕ በማሸግ ማኀተምእናፊርማ በመፈረም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፣

5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያ ናሙና ማቅረብ እንዲሁም የፈርኒቸር ናሙና በፎቶ ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. የፈርንቸር፣ጥገና እና የኤሌከትሮኒከስ ጥገናን በተመለከተ በአካል በመገኘት ያለበትን ደረጃ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎችን ሚ/አ /ጤ/ሳ/ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር 0473360763 መጠቀም ይችላሉ፡፡

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Save Tender