የ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የውሃ መሳቢያ ፓምፕ፣ ጋርመንት እና የግብርና ማሽነሪዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የውሃ መሳቢያ ፓምፕ፣ ጋርመንት እና የግብርና ማሽነሪዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾችን
1. የተጫራች እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
3. በፋይናንስ መ/ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል።
4. ለእያንዳንዱ የተዘጋጀ ጨረታ አይነት ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላል።
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለየብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለኢያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፕ የውጭ ገፅ ዋና /ኦርጂናል/ ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በቀጣይ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 16ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለውሃ መሳቢያ ፓምፕ 113,000 (አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ብር) ለጋርመንት እና ለግብርና ማሽነሪዎች 96,000 (ዘጠና ስድስት ሺህ ብር) ሲፒኦ ባንክ ጋራንቲ ወይም ቼክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 181 0500 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ
መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመ/ቤቱ አድራሻ ከመድኃኒዓለም ቤተከርስቲያን ፊት ለፊት
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ
