Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address ደ/ብርሃን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline15 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-15 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Metals And Metal Working

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለ 40 ጫማ ኮንቴነር መሸጥ ይፈልጋል

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአፈ/ከሣሽ አቶ ፀጋዬ ያረጋል እና በአፈ/ተከሣሽ ናንቶንግ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ኃ/የተ/የግል ማህበር መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን ተከሳሹ ለመጨረሻ ጊዜ ሲሰራበት በነበረው በደ/ብርሃን ከተማ አስ/ጠባሴ ክ/ከተማ አዲስ ገነት ቀበሌ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የአፈጻጸም ተከሳሽ ንብረት የሆነውን እና ከውጪ ሀገር እቃ ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውል አንድ ባለ 40 ጫማ ኮንቴነር በግምት መነሻ ዋጋ 1,095,779.00 (አንድ ሚሊዮን ዘጠና አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ንብረቱ በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውስጥ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።

ስለዚህ -

1.        ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 08 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 አስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል።

2.       ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እና የግምቱን 1/4ኛውን ዋጋ በሲፒኦ ለሐራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።

3.        ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት እንደፍርዱ ለማስከፈል ነው።

4.        ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን፣ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል፤ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሐራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።

5.        የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።

 

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE