Tender Detail

Tender Details

  • Company የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-12-04-86-80
  • Website
  • Deadline13 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-13 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Construction Works

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሙዱላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልገሎት ጽ/ቤት የሙዱላ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን መንገድ ግንባታና የዲች ግንባታ መ/ቤታችን ከመንግሥትና ከህብረተሰብ ተሳትፎ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሙዱላ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የዲች ግንባታ በማካሄድ የህብረተሰብ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የልማት ሥራዎችን በመስራት ከዚህ

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሙዱላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልገሎት ጽ/ቤት የሙዱላ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን መንገድ ግንባታና የዲች ግንባታ መ/ቤታችን ከመንግሥትና ከህብረተሰብ ተሳትፎ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሙዱላ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የዲች ግንባታ በማካሄድ የህብረተሰብ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የልማት ሥራዎችን በመስራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዲች ግንባታና ኮብልስቶን ንጣፍ ሥራ ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት:

1.     ከአቶ ተሰማ ጂሞሬ እስከ አቶ ኤልያስ መንገሻ ሎት 1 የዲች ግንባታ ሥራ 206 ሜ

2.     ከአቶ ወመጎ ወርቅነህ እስከ አቶ አብርሃም አሻሞ ሎት 2 የዲች ግንባታ ሥራ 121 ሜ

3.     ከአቶ ሀ/ሚካኤል አኒቶ እስከ አባያ ጎርጅ ሎት 3 የዲች ግንባታ 200 ሜ

4.     ከአቶ ፍቅሬ ኦልኪሶ እስከ ጴጥሮስ አየሞ ሎት 4 የዲች ግንባታ 135 ሜ

5.     ከቀድሞ ሙስሊም መቃብር እስከ አዲሱ ማናኸሪያ 153 ሜትር ኮብልስቶን ለማሠራት ስለፈለግን ሥራው በቀጠይ በአስቸኳይ ማሰራት እንዳለበት ከከተማ አስተዳደሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መነሻ ሥራ ዝርዝር (Bill of Quantity) በወጣው መሠረት ጨረታው የፋይናንስን ደንብንና መመሪያን በጠበቀ መነሻ ለማሠራት በመለየት ወደ ሥራ እንዲገቡ እያሳሰብን

ለዲች ግንባታ ማሟላት ያለባችሁ

•        ለዲች ግንባታ GC ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ፣ የንግድ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፣ -የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ ወቅታዊ የመልካም ሥራ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፣ ከከተማ አስ/ርፋይናንስ የመጠናቀቁን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፣ ሂሳብ ስህተት ከሁለት ፐርሰንት /2%/ በላይ ከሆነ ከጨረታ ውድቅ ይደረጋል።

•        ሳይት ምልከታ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣ ከመሐንዲስ ግምት 15% ከፍም ሆነ ዝቅ ያለው ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡ ቅድሚያ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ትንታኔ ሳያደርግ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ውድቅ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ የተረጋጠ CPO ከቫት በፊት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

•        በየትኛውም ከተማ አስተዳደር በጨረታ አሸንፎ በሥራ ላይ ያለ ድርጅት ለመወዳደር ከከንቲባ ጽ/ቤት መጨረሱን የሚገልጽ የግምገማ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም።

•        ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነድ ወይም ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ዋና እና ኮፒ የተሰራ ማስረጃ ዋና እና ኮፒ በተለያዩ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ፈርማ እና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። አሸናፊ የሆነው ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ዋስታና በጥሬ ብር ማቅረብ አለበት፡፡

•        ሳይት የተጀመረ ሥራ መጨረሱን የድጋፍ ደብዳቤ ከአደራጅ መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችል፣ አሸናፊ የሆነው ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል።

ለኮብልስቶን ግንባታ ሥራ ማሟላት ያለባችሁ

1.     ለኮብልስቶን ስራ የኮብልስቶን ጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ፍቃድ ያለው፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት

2.     ከእነዚህ ውጪ ያሉ ለዲች ሥራ የተዘረዘሩ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ለኮብልስቶን መስፈርትነት ይሆናሉ።

–       ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከሙዱላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡

–       ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ ላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት ዋጋውን ያለምንም ስርዝ ድልዝ በአሃዝና በፊደል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ጨረታ በታዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ከ12/05/18 እስከ 02/06/2018 ዕለቱ ሰኞ 15ኛው ቀን ማለትም 6:30 ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ-

•        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

•        ህጋዊ ተጫራቾችና ፍቃድ ያላቸውና አላይን ላይ የተመዘገበና ቲን ነምበር ያላቸው በዕለቱ ተጫራቹ በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 09-12-04-86-80 መጠቀም ይቻላል፡፡

 

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender