Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
  • Address 6ኪሎ አካባቢ ከፈረንሳይ ታክሲ መያዥ አለፍ ብሎ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111261615
  • Websitehttps://aaceb.gov.et/
  • Deadline06 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-06 00:00:00
  • Categories Education And Training , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት 01 የተማሪዎች ውጤት መግለጫ ካርድ ህትመት፣ ሎት 02 የደንብ ልብስ ስፌት እና ሎት 03 ዓመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሔት ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት 01 የተማሪዎች ውጤት መግለጫ ካርድ ህትመት፣ ሎት 02 የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 03 ዓመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሔት ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2.     ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ለሎት 01 ብር 50,000.00፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 ብር 10,000.00 ጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከቢሮአችን ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና በዚያው ክፍል በሚገኝ ከግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነዱን በሶፍት ኮፒ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ።

4.     ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ሎት 01 እና 03 ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ ለሎት 02 ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ በመለየት አሟልቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት / ለዚሁ : ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤

5.     ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን / በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።

6.     የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣

7.     የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ አስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወደ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

8.     አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት እቃዎችን እና አገልግሎት ቢሮው በመረጠው ቦታ እና መጋዝን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡

9.    ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ- በስልክ ቁጥር 011 122 64 56

አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender