Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0911-66 49 88
  • Website
  • Deadline05 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-05 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር ዲስትሪክት በገነባው የአዘዞ-ጎንደር አስፋልት መንገድ ላይ የትራፊክ መስመሮችንና ልዩ ልዩ ምልክቶችን በቂ ልምድ ባለው ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማስቀባት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ

የግዥ መለያ ቁጥር GN-022/2018

 

የመንገድ ላይ የትራፊክ መስመሮች መቀባት የአገልግሎት ግዥ

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር ዲስትሪክት በገነባው የአዘዞ-ጎንደር አስፋልት መንገድ ላይ የትራፊክ መስመሮችንና ልዩ ልዩ ምልክቶችን በቂ ልምድ ባለው ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማስቀባት ይፈልጋል።

መ/ቤታችን ለስራው የሚያስፈልገውን ቀለም የሚያቀርብ ሲሆን ከቀለም ውጭ ያሉ ለስራው የሚያስፈልጉ ሌሎች ቁሶች፣ ማሽኖች፣ የሰው ሀይልና የመሳሰሉት በተጫራቹ የሚቀርቡ ናቸው።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘረፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ እና ከዚህ በፊት ስለፈፀሟቸው ስራዎች የመልካም ስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 በመክፈል መግዛትና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ላሉት 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4:30 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

የጨረታ ሰነድ በዋናው መ/ቤት ዕቃ ግዥ ቡድን አንድና በዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ይቻላል።

መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 66 49 88 / 09 91 18 36 57 መደወል ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender