የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል L110cc በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል L110cc በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም -
➢ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
➢ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ 10,000 (አስር ሺህ) ብርማስያዝ አለባቸው::
➢ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
➢ የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሽገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
> ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው የስራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ቦታ ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት እያግደውም፡፡
➢ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይበተገለፀው ቦታና ሰአት ይሆናል፡፡
➢ ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል፡፡
➢ አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው:: በቁጥርና በፊደል ከተገለጸው የዋጋ መጠን ልዩነት መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ቢሮው የተሻለ አማራጭ አገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፣ ብሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
