የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል
የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የእንስሳት መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከቢሾፍቱ ግብርና ምርምርማዕከል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
❖ ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የ2018 የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርቴፍኬት፣የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ጨረታ ለመካፈል የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ በአቅራቢነት ዌብ ሳይት የተመዘገቡበት ኮፒ እና ለተጫረቱበት መኖ ናሙና በማቅረብ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዕከሉ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ 25/5/ 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው::
❖ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በተመሳሳይ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
❖ የጨረታ ሳጥን 25/5/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዋ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
❖ ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0114339472
የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል
