የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04-2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የአገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን ምርመራ |
ምርመራ
|
|
1 |
የመኪና ኪራይ |
10,000.00 |
|
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቲን /Tin/ ሰርተፍኬት እና ክሊራንስ ማስረጃ እንዲሁም ሶስተኛ ወገን፣ ቦሎ እና ኢንሹራንስ የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ተሽከርካሪ ጥራትና ቁመና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ተቋማችን በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት የፋይናንስ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት አቅርበው በጥራት ኮሚቴ ቴክኒክ ምርመራ የሚካሄድ ይሆናል።
3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ሕንጻ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-04 ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት 10ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 10-08 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ 10ኛ ፎቅ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0911002020/0913727549 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
