Tender Detail

Tender Details

  • Company Get As International Plc /ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር/
  • Address ቃሊቲ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911240050
  • Websitehttps://getasplc.com/
  • Deadline29 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Used Items , Vehicle

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

Get As International Plc /ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር/


ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል:: የጨረታ ሰነዱን በጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቃሊቲ ትራንስፖርት ዩኒት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት 01 ኦሪጂናልና 01 ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል:: ጨረታው የሚከፈተው ከ10ኛው ቀን ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- ተሽከርካሪዎቹን መመልከት የሚፈልግ ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ዕለት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት መመልከት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። አሸናፊ ተጫራቾች በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ የተሽከርካሪውን ክፍያ አጠናቆ የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ሲቀር ጨረታው ውድቅ ሆኖ ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ በ07 ቀናት ውስጥ ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል።

ድርጅቱ፡- የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቃሊቲ ትራንስፖርት ዩኒት

ስልክ:- 09-11-20-52-94/09-10-46-43-69/09-23-27-13-49

Save Tender