Tender Detail

Tender Details

  • Company ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address ወላይታ ሶዶ መናኸሪያ ፊት ለፊት ወደ ኦቶና በሚወስደው አስፋልት ላይ ሙሐባና ቻይና ጋራዥ ጎን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 551 0642
  • Website
  • Deadline24 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-26 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

ዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን 2018 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከሱራ ኮዮ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ዳፕ/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን


3ኛ ዙር የወጣ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 008/2018

 

ዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን 2018 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከሱራ ኮዮ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ዳፕ/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

በዚሁ መሰረት

1.     በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ ያላት/፤

2.     ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤

3.     ከዚህ ቀድሞ በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፤

4.     የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤

5.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6.     በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤

7.     ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 2,400 /ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል/ በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሠሌዳ ቁጥር የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ብቃት ማረጋገጫ ከትራንስፖርት ቢሮ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

8.     የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር /1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤

9.     የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።

10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ7ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት በመስፈርቱ መሠረት ማሸነፉ ሲረጋገጥ በዩኒዬን ማስታወቂያ ቦርድ የሚገለፅ ይሆናል።

 

አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ መናኸሪያ ፊት ለፊት ወደ ኦቶና በሚወስደው አስፋልት ላይ ሙሐባና ቻይና ጋራዥ ጎን ይገኛል።

ስልክ ቁጥር፡- 046 551 0642/ 09 10 43 25 49/09 20 98 61 19

ፋክስ፡- 046 552 2955

 

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን

ወ/ሶዶ

Save Tender