Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ
  • Address ደቡብ ጎንደር ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0584 41 14 79
  • Website
  • Deadline02 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-02 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2018/19 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የዳፕ እና ዩሪያ በድምሩ 945,961 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው በጎሕ ዩኒየን በስሩ ባሉ ወደ 205 መሰረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸው የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ


የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2018/19 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የዳፕ እና ዩሪያ በድምሩ 945,961 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ካለው በጎሕ ዩኒየን በስሩ ባሉ ወደ 205 መሰረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ማለትም ፡-

1.     ከነፋስ መውጫ፣ ከመካነ ኢየሱስ፣ ከደብረ ታቦር፣ ከወረታ፣ ከደራ ሃሙሲት እና ይፋግ ማዕከላዊ መጋዘን በስሩ ባሉ 205 መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸው የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው 6 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ለዚህም በሥራው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማኅበር (አ.ማ) በአዲሱ አደረጃጀት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የምትችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎ ዝርዝር መሰረት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡-

1.     የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር (ቢሮ) የታደሰ ንግስ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው።

2.     የገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት(ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆኑ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት መረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበ የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5.     የተሽከርካሪ ዝርዝር (ተ.ቁ) የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው አይነትና የመጫን አቅሙ የሚያስረዱ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ወይም ከክልል መንግሥት ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.     የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነትና መጠን በኩንታል እንዲሁም ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

8.     ተጫራቾች በጎሕ ዩኒየን ስም የማይመለስ ብር 300.00 ብር በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ገንዘብ መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይቻላል።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጎሕ ዩኑየኑ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረብ ጋር በማሸግ በደቡብ ጎንደር ግብርና መምሪያ በግብርና ግብዓት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ቁር 10 በተዘጋጀላቸው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሳጥኑ ውስጥ በማስገባት በእለቱ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. የሞላችሁትን የጨረታ ሰነድ በ16ኛው ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት 7፡30 ተዘግቶ በደቡብ ጎንደር አስ/ዞን ግብርና መምሪያ የስብሰባ አደራሽ 8፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

12. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁር 10 ደረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0584 41 14 79 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ

Save Tender