የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለሀሩማህ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰጠውን የማር ውጤቶች ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለሀሩማህ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰጠውን የማር ውጤቶች ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚሸጠው ንብረት |
የጨረታው መነሻ ዋጋ
|
ጨረታው የሚከፈትበት |
||||
|
|
የማር ውጤቶች ማቀነባበሪያ ማሽኖች ዝርዝር፡- |
የሚገኝበት አድራሻ |
ብዛት
|
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
|
|
1 |
1. Bee wax processing machineries. 2.Honey processing machineries. 3. Honey filling Machine. 4. Honey packing machine and accessories. |
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ፡-08 |
1 |
ብር 6,383,248.85
|
ጥር 26 ቀን 2018 ዓ/ም
|
4:00- 6:00
|
ፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ
|
የጨረታው መመሪያ፡-
• ንብረቶችን ለመግዛት የሚፈልግ የሚገዛበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይችላል።
• ተጫራቾች የንብረቱን መነሻ ዋጋ 20% በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በታሸገው ፖስታ በተጨማሪነት ማስገባት ይገባል።
• ማሽነሪው የተተከለ ሲሆን የሚሸጠው ማሽኑ ብቻ በመሆኑ አሸናፊው ከአሸነፈ በኋላ ማሽነሪውን ማጓጓዣ ወጪ የሚሸፈነው ነቅሎ የመውሰድ ኃለፊነት ያለበት ሲሆን የማሽነሪውን መንቀያ እና ማጓጓዣ በአሸናፊው ነው።
• የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
• ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
• አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል፡፡ መስፈርቱን ለማያሟሉ ሽያጩ በካሽ ይሆናል።
• አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ አጠቃሎ መክፈል አለበት፡፡ ካልከፈለ ባንኩ ጨረታውን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ በድጋሜ ሲካሄድ የንብረቱ መሸጫ ዋጋ ከቀነሰ ልዩነቱን ይከፍላል።
• ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 058-178-66-49
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት
