Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር መቀሌ
  • Address መቀሌ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 034 241 57 58
  • Website
  • Deadline01 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-01 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Vehicle

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሎት አንድ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና ሎት ሁለት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር መቀሌ


ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሎት አንድ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና ሎት ሁለት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩትን በማሟላት እቃዎቹ በሚገኙበት የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች በመገኘት ዕቃዎቹን እና ተሽከርካሪዎችን በመመልከት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በገዙበት የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች የጨረታ ሰነዱን አሽገው መመለስ አለባቸው።

ጨረታው የሚከፈተው የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ16ኛው ቀን ነው። የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ ልክ 8፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

ማስገንዘቢያ፡-

1.     ጨረታው የሚከናወነው በዚህ ማስታወቂያ በተገለጹት የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች በመሆኑ በሁለቱም ሎት ማብራሪያና ጥያቄ ሲኖር መጠየቅ ይቻላል። በሁለቱም ሎት መወዳዳር የምትፈልጉ ሰነድ ሞልታችሁ ስታስገቡ ለየብቻ ሎት አንድ እና ሎት ሁለት ብላችሁ ይሆናል። ለአጠቃላይ ማብራሪያ አዲስ አበባ ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር ፊትለፊት በስልክ ቁጥር፡- 0111232705 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘትይችላሉ።

2.     የጨረታው መከፈቻ 16ኛው ዕለት የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተመለከተው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

3.     በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚመለስ ለሎት አንድ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) እና ለሎት ሁለት 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ በማስያዝ መሳተፍ ይችላሉ።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መሙላት አለባቸው። አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Save Tender