በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የዶ/ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ባለው በጀት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን እና ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ዶክተር ካርል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የዶ/ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ባለው በጀት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ
የእንጨት ሥራ ዲፓርትመንት እቃዎችና ግብዓቶችን፣
የሕንፃ መሣሪያዎችን እና ግብዓቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣
የፅዳት ዕቃዎች፣ የእስቴሽነሪ ማቴሪያሎችን የልብስ ስፌት አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፣
የብረታብረት ዲፓርትመንት አላቂና እና ቋሚ እቃዎች
እንዲሁም ሌሎች ለተማሪዎች ማሠልጠኛ የሚሆኑ አላቂ እቃዎችን እና ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችል
2. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
4. የግዥው መጠን ብር 200.000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ -የተጨማሪ እሴት ታክስ NATI ከፋይነት የተመዘገቡ
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው”
6. የእቃው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዶች ማግኘት ይቻላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር ብቻ/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን 9/5/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በዶ/ር/ ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮ ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ።
8. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆየው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 9/5/2018 ዓ.ም. ላይ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ የሚሰላ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በዶ/ር/ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በሚያዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 25/5/2018 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዶ/ር/ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ25/5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በዶ/ር/ካ/ቴ/ሙ/ማ/ኮ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር 011 890 6003/011 624 0221/22/23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
➢ አድራሻችን ከአዲስ አበባ 125 ኪሜ ከደብረ ብርሃን 74 ኪሜ ከአዲስ አበባ - ደብረ ብርሃን በሚወስደው መንገድ ከሰንቦ 26 ኪ.ሜ ገባ ብሎ እንገኛለን አሳግርት ወረዳ ጊና አገር
ዶክተር ካርል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ
