Tender Detail

Tender Details

  • Company የሸ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሰረት ልማት ጽ/ቤት
  • Address ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የሽ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎት ጽ/ቤት ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

የሸ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሰረት ልማት ጽ/ቤት


የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

 

1.     የጨረታው ዙር ...17ኛ

2.     የጨረታው አይነት...መደበኛ

3.     የሽ//ከ/አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ይህንኑ አዋጅ ለማስፈጸም የአብክመ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ "ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታው ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሸ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

4.     ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።

5.     ተጫራቾች ሁለት የተለያየ ፖስታዎችን በማዘጋጀት ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውስጥ በመለየት ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሦስት የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን እንዲሁም ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በሰም ወይም በአካባቢው በሚገኝ ማጣበቂያ በማሸግ እና ፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ9/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው / አስረኛው/ ቀን 11 ሰዓት ማለትም 22/05/2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ለጨረታ ተግባር በተዘጋጀው ቦታ ኦርጂናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እና ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6.     ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 09/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን 22/05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።

7.     የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና አሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ 3 ሰዓት ሳይ ይከፈታል።

8.     ጨረታው ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሸ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 22/05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

9.     ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በጽ/ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም የሸ/ከ/ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

10.  መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- በግልፅ የማይነበቡ ስርዝ ድልዝ ያለባቸው ሰነዶች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።

 

የሽ/ከ/አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎት ጽ/ቤት

Save Tender