Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline26 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-26 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Security Service

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት-1 የጥበቃ አገልግሎት እና በሎት-2 የጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2018

 

1.     የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት-1 የጥበቃ አገልግሎት እና በሎት-2 የጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች/የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

3.     ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ የከፈሉበትን ደረሰኝ በማሳየት እና በመመዝገብ መውሰድ ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን አገልግሎቶች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሰንጠረዥ መሰረት ለ90 /ዘጠና/ ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

 

የሎት ቁጥር

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን (በብር)

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

ሎት-1

የጥበቃ አገልግሎት ግዥ

ብር 10,000.00

ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት

ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት

ሎት-2

የጽዳት አገልግሎት ግዥ

ብር 10,000.00

 

6.     ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7.     ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Save Tender